ያፈረስኩት ጎጆ

Mekdes Jemberu

የቤቴ ጠቀራ . . .
    አቧራው ብናኙ
ለሠራሁት ሥራ . . .
    ምስከር እማኙ
መራቄን አየና
ሆኜ ተቀምጨ እንደጠል ዳመና   ::
መጥቶ ተመረገ . . . ጉድፋን ደነጎረ
ዓይኔን ሊያሳክከኝ . . . እየቆረቆረ  ::
የተጋደምኩት ርብራቡ ብዙ . . . ደልደላ ምንጣፉ
ዙሪያ ዝምዝማቱ . . . ውብ አቀናነፉ
    አሾህ ተሰካበት . . .
ትቸው የመጣሁት . . . ጠልቸው የራቅኩት
    ብናኙ ትናኙ . . . የቤቴ ጠቀራ
አላይህም ያልኩት . . . አላውቅህም ያልኩት
    ምላሽ የነፈግሁት . . . ቢጣራ ቢጣራ
ጉልጥምት አበጅቶ   :
ጥርስ ጥርስ አውጥቶ  :
    ጎኔን ጠበሰቀኝ . . . ከአለሁበት መጥቶ
ከተጋደምኩበት ጦሩን ይዞ መጣ . . .
    ትዝታውን ሰብቆ
በወና ኮረብታ . . . ድምጹን እያወጣ . . .
    በድኑን እያሳየኝ . . . አካሉን አርቆ
ስሜን እያወጀ . . . ግብሬን እያሳጣ
    ከተበዘበዘው ከድንኳኔ ዘልቆ
አመጣብኝ ደግሞ . . . አርፌ እንዳልተኛ
    ጎኔ እንደደቀቀ   :
ፀፀቴን አየና . . . ሆኜ ሀዘንተኛ
    ወስዶ እየመለሰ . . . አቅርቦ እየራቅ
ኮረብታ ጉድጓዱ . . . ስንጥቅጥቅ መሬቱ
    ገደል ገመገሙ   :
ጥሻ መሽሽጊያው . . . ቁልቁለት ዳገቱ
    ጉበኑ ግርግሙ  :
እየተማከሩ . . . በእኔ አየዶለቱ
በኔ እየተስማሙ
እየወጉት ጎኔን . . . ሰይፍ እየመዘዙ
    በትዝታ ሳንጃ
ፀፀት አፀንሰው . . . ብሶት አስረገዙኝ
    አጣሁ ማስወገጃ
ማስተዋል ተስኖኝ . . . መንቅሬ የጣልኩት
    እንደቃ ጨዋታ   :
ጊዜያዊ ቻቻታ . . . አሳጥቶኝ ተስተካከሎ ራሱን
    ቀልሶ
የናቅኩት ትዳሬ ቢንቀኝ መልሶ
ምጥ እንደያዛት ቤት . . . ጭንቄ እየተነሣ
    ሰዓት በጨመረ
እንደሞት ፍርደኛ . . . አካሌ እየሳሳ
    ቀን በተቆጠረ
መነሻ እንደሌለው . . . ወድቆ እንደተረሳ
    ቀለሜ ረገፈ . . . ቅሳሜ ተሰበረ
የቤቴ ጠቀራ  . . .
እንደባሕር ሞገድ . . . ድምፁ እየተመመ
    ብቅ እልም እያለ
በእኔ እየፎከረ . . .  በኔ እየፈለመ
    ትውስታውን ሳለ
ጉድፍ ሆኖ ገብቶ
ዳግሚያ ቆረቆረኝ መረቡን ዘርግቶ
     . . . በኔ ላይበርትቶ   ::